Skip to content

የ2014 ዓ.ም የትንሣኤ በዓል አከባበር እና የቅዱሳን መካናት መንፈሳዊ ጉብኝት

በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሃዱ አምላክ አሜን

በቅድስት ሀገር እየሩስሳሌም አማን ኢትዮጲጲያ እሰጎብኚ እና የጉዞ ወኪል ድርጅት የ2014 ዓ.ም የትንሣኤ በዓል አከባበር እና የቅዱሳን መካናት መንፈሳዊ ጉብኝት ዝርዝር መርሃ ግብር፡፡

1.ሚያዚያ 14/2014 ዓ.ም ረቡዕ(April 20 2022)

በቅድስት ሀገር እየሩሳሌም የትንሣዔን በዓል ለማክበር ከኢትዮጲያ የሚመጡ አትዮጲያዊ ምዕመናን በእስራኤል አለማቀፋዊ አውሮፕላን ማረፊያ( ቤን ጎሪዮን የአውሮፕላን ጣቢያ) በመገኘት በቬርድ ሃሻሮን የጉዞ ወኪል ተወካይ ለእንግዶቹ ወደ ቅድስት ሃገር የእንኳን ደህና መጣችሁ አቀበባል ይደረጋል፡፡ እንግዶቹም በተዘጋጀላቸው አውቶበስ ሁነው ወደ እየሩሳሌም ይጓዛሉ በተያዘላቸውም ሆቴል እረፍት ያደርጋሉ፡፡

2.ሚያዚያ 15/2014 ዓ.ም ሀሙስ (April 21 2022)

 • ጌታ የመጨረሻውን አራት ያበላበት፣ የሐዋርያትን እግር ያጠበበትና ለሐዋርያት መንፈስ ቅዱስ ያወረደበትን ቦታ ጽርሐ ጽዮንን ይጎበኛሉ፡፡
 • የዳዊት መቃብር ወደ ሚገኝበት ክፍል በመውረድ መቃብሩን ይጎበኛሉ
 • ጽርሐ ጽዮን ቤተክርስቲያን እመቤታች ን ቅድስት ድንግል ማርያም የግንዘት ቦታ በመሄድ ይጎበኛሉ
 • በቅድስት ሃገር ቀደምት ኢትዮጲያ ገዳም በሆነው ዴር ሱልጣን ገዳም በመሄድ በአርብዒቱ እንስሳ የመድኀኒዓለም ቤተክርስቲያን በሚካሄደው የጸሎተ ሐሙስ ሕጽበተ እግር ሥርዓተ ጸሎት ላይ ተገኝተው በረከት ይቀበላሉ ፡፡ ሥርዓተ ቅዳሴው ከአለቀ በኋላዳ ኆጼል በመመለስ አራት ተመግበው እረፍት ያደርጋሉ፡፡

3.ሚያዚያ 16/2014 ዓ.ም ዓርብ (April 22 2022)

 • ምዕመናን ወደ ጌቴ ሴማኒ በአውቶብስ ተጉዘው ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ የጸለየበትን አጸደ ሐመል /የአታክልቱን ቦታ/ ይጎበኛሉ፡፡
 • አጸደ ሐመል ወረድ ብሎ በዚያው በጌቴ ሴማኒ የሚገኘውን የእመቤታችን የማርያም መቃብር እና በክብር ያረገችበትን/ፍልሰታ ለማርያም/ ቦታ ይጎበኛሉ፡፡
 • 38 ዓመት በአልጋ ላይ የነበረው መጻጉ ወደ ተወፈሰበት ቦታ ቤተ ሳይዳ በመሄድ የመጠመቂያውን ቦታ እና በቅድስት ሐና ስም የታነጸውን ቤተመቀረደስ ታሪካዊ ይዘት እየተመለከትን ገለጻ ይደረጋል፡፡
 • የጌታችን የመድኃኒታችን የኢየሱስ ክርስቶስ ፍኖተ መስቀል የመጀመሪያ ምዕራፍ ከሆነው የጲላጦስ አደባባይ በመጀመር 14ቱን ምዕራፎች ወይም ፍኖተ መስቀል እያዩና ገለጻ እየተደረገላቸው መዳረሻቸው የኢትየፒያ ገዳም ዴር ሱልጣን ይሆናል፡፡
 • በመጨረሻም በዴር ሱልጣን በኢትዮጲያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ገዳም ውስጥ ግብረ ህማማቱን በመስማትና በስግደት አስከመጨረሻው የጥብጠባና የበዓሉ ዑደት አስኪጠናቀቅ ድረስ በገዳሙ በመቆየት የስቅለት በዓል ፍጻሜ ሲሆን ወደ ሆቴል በመመለስ እረፍት ይደረጋል፡፡

4 .ሚያዚያ 17/2014 ዓ.ም ቅዳሜ (April 23 2022)

 • በእለቱ የቄጠማ በዓሉን ከአከበርን በኋላ ቀጥታ ጉዞ ወደ ደብረ ዘይት ተራራ በማድረግ ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በቤተ ፋጌ አህያዎቹ የታሰሩበትን ሥፍራና በኣህያዋ ውርንጭላ ተቀምጦ የሆሳዕናን ጉዞ የጀመረበትን ቅዱስ ስፍራ ይጎበኛሉ፡፡
 • ሐዋሪያዎች ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ እንዴት እዲጸልዩ በጠየቁት መሰረት አባታችን ሆይ የሚለውን ጸሎት ያስተማረበትን ቅዱስ ስፍራና ጌታ ያድርበት የነበረበትን የኤሌዎንን ዋሻ ይጎበኛሉ፡፡
 • በመቀጠልም ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በሐዋርያት መካካ በክብር ወደ ሰማይ ከፍ ከፍ እያለ ያረገበትን ቦታ ይጎበኛሉ፡፡
 • ወደ ሰበን አርክ በመሄድ ኢየሩሳሌምን በሚያሳየው አደባባይ ላይ በመሆን ስለ ጥንቷ የዳዊት ከተማ፣ ሞሪያ ተራራ፣ ጌታ ስለ ኢየሩሳሌም መፍረስ ያለቀሰበትን ቦታ በመጎብኘት ወደ ሆቴል መልስ ይሆናል፡፡
 • ከእለቱ ጉብኝት በኋላ ወደ ሆቴል በመመለስ መጠነኛ እረፍት በማድረግ 2፡00 ሰዓት ላይ ለትንሳኤው በዓል ተዘገጃጅተው ምዕመናኑ በመረጡት በዴር ሱልጣን የኢትዮጲያ ገዳም እና በደብረ ገነት ቅድስት ኪዳነምህረት ገዳም በመገኘት የትንሳኤውን ሥርዓት ይከታተላሉ ያስቀድሳሉ፡፡

5.ሚያዚያ 18/2014 ዓ.ም ዕሁድ  (April 24 2022)  በዓለ ትንሣኤ

ምእመናኑ ከሌሊት ድካማቸው እስከ ምሣ ሥዓት እረፍት አድርገው ከቆዩ በኋላ የፋሲካን በዓል ለማክበር በተዘጋጀላቸው ልዩ የምሳ ፕሮግራም ይሄዳሉ በአስጎብኚ ድርጅቱ መስተንግዶ ይካሄዳል፡፡ ከምሣ በኋላ ወደ ሆቴላቸው በመመለስ እረፍት ያደርጋሉ እራትና አዳር በሆቴላቸው ይሆናል፡፡

6.ሚያዚያ 19/2014 ዓ.ም ሰኞ  (April 25 2022) ማዕዶት

 • ጧት ምእመናን በሆቴላቸው ቁርስ ከበሉ በኃላ አይንከርም በመሄድ መጥምቁ ቅዱስ ዩሐንስ የተወለደበትንና የእመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ኤልሳቤጥን ልትጠይቃት በሄደችበት ግዜ እመቤታችንነና ኤልሳቤት ተገናኝተው ሰላምታ የተለዋወጡበትን ገዳም ይጎበኛሉ፡፡
 • በቀጣይ የጌታ መልዓክ ለእረኞቹ የዓለም መድኃኒት ኢየሱስ ክርስሮስ በቤተልሄም እደተወለደ የምስራቹን ለእረኞቹ ወደ አበሰረበት ኖሎት ተብሎ ወደሚጠራው ሥፍራ በመሄድ ከጎበኙ በኋላ የምዓ ፕሮግራም በቤቴልሄል ሆኖ
 • ከምሣ በኋላ የወተት ዋሻ ፣ የኢትዮጲያ እየሱስ ገዳም ጌታችን መዳኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በተወለደበት ቅዱስ  ስፍራ በቤቴልሄም ዋሻ በመገኘት ጸሎት አድርገውና ጎብኝተው የመልስ ጉዞ ወደ ኢየሩሳሌም በማድረግ እራትና እረፍት በሆቴላቸው ይሆናል፡፡

7. ሚያዚያ 20/2014 ዓ.ም ማክሰኞ  (April 26 2022)

 • ጉዞ ወደ ዮርዳኖስ ወንዝ በማድረግ ምእመናን የበረከት ጥምቀት ይጠመቃሉ
 • ከቁርስ በኋላ ጉዞ ወደ ኢያሪኮ በማምራት ስለ እሩሩህ ሳምራዊ ጌታ በምሳሌ ያስተማረበተና /ሉቃ10÷25-37/ ጌልጌላ እና ስለ ቤት አራባ ታሪካዊ ቦታዎች በመንገድ ገለፃ እየተደረገላቸው ወደ ገዳመ ቖሮንጦስ በመውጣት ጌታችን የጸለዬበትንና የጾመበትን ቅዱስ ስፍራ ይጎበኛሉ፡፡ማቴ 3÷13-15፣ ማር 1÷9-11፣ ሉቃ 3÷21-22
 • ስለጥንታዊቷ እያሪኮ ገለፃ እተደረገላቸው በዛው የሚገኙትን የኤልሳ ምንጭ በኢያሪኮ የሚገኘውን የኢትዮጲያ የቅዱስ ገብርኤል ገዳምና የዘኬዎስን ዛፍ ከጎበኙ በኋላ የምሳ እረፍት ይሆናል፡፡
 • ከምሳ በኋላ ወደ ሙት ባህር በመሄድ ምእመናን በውሃው ይታጠባሉ ወይም ይዋኛሉ፡፡ ከዛም መልስ ወደ ኢየሩሳሌም ሆኖ በሆቴላቸው እራ በልተው እረፍት ያድራገሉ፡፡

8. ሚያዚያ 21/2014 ዓ.ም ረቡዕ (April 27 2022)

 • ጎብኚዎች ጧት ቁርስ ከበሉ በኋላ ወደ ጎለጎታ በመሄድ የጌታን የመቃብርና ትንሳኤ ቦታን ተሳልመው በአሮጌው ከተማ የሚፈልጉትን እዲገዙ እስከ ምሳ ሥዓት የገቤ ግዜ ይኖራቸዋል፡፡ ከምሳ በኋላ እደሚኖረው የግዜ ሁነታ በኢየሩሳሌም እና በዙሪያዋ ያልተጎበኙ ቦታዎችን ይጎበኙና ወደ ሆቴላቸው ይመለሳሉ፡፡
 • በሆቴላቸው እራት ከበሉ በኋላ ለቀጣዩ የሰሜን እስራኤል ጉዞ ዝግጅት ያደርጋሉ፡፡

9. ሚያዚያ 22/2014 ዓ.ም ሐሙስ (April 27 2022)

 • ጎብኚዎች ጧት ቁርስ በልተው የሆቴላቸውን ቁልፍ በማስረከብ ጉዞ ወደ ሰሜን እስራኤል ታቦር ተራራ ያደርጋሉ፡፡
 • ጎብኚዎች በታቦር ተራራ ሲደርሱ ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በህርዬ መለኮቱን የገለፀበትን የላቲን ገዳም ይጎበኛሉ፡፡
 • ቀጣይ ጉብኝት ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በሰርጉ ቤት የመጀመሪያውን ተአምራት ወደፈጸመበት ቅዱስ ስፍራ ቃና ዘገሊና ይሆናል፡፡
 • ከምሳ በኋላ ጉብኝቱን በመቀጠል ናዝሬት የማርያም ምንጭ እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም የመልአኩን ብስራት የሰማጭበትን፣ የብስራቱን ቤተመቅደስና ቤተ ዮሴፍን ይጎበኛሉ፡፡ በመጨረሻም ጉዞ ወደ ቲበሪያ በማድረግ በተያዘላቸው ሆቴል በመሄድ ክፍላቸውን ከያዙ በኋላ እራት በልተው እረፍት ያደርጋሉ፡፡

10. ሚያዚያ 23/2014 ዓ.ም አርብ (April 28 2022)

 • ጌታ መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ የተራራው ስብከት  (አንቀጸ ብፁዓን) ያስተማረበትን ቅዱስ ስፍራ ይጎበኛል በዚሁ ስፍራ ትምህርት ይሰጣል፡፡
 • ወደ ቅፍቸናሆም በመሄድ ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ያስተምርበት የነበረውን የአይሁድ ቤተ ሙክራብ፣ የሐዋርያው የቅዱስ ጴጥሮስ፣ የሐዋሪያው የእዲሪያስ፣የሐዋሪያው ያዕቆብ፣ የሐዋሪያው የቅዱስ ዩሐንስ፣ የቀራጩ የማቴዎስ ፣ ብላቴናው የታመመበት የመቶ አለቃና ከዛም ጌታ ይኖርበት የነበረበትን የቅፍርናሆም መንደር ፍርስራሽ ይገኛሉ፡፡
 • ከቅፍርናሆም ጉብኝት በመቀጠል ጌታችን ሰሦስተኛ ግዜ ለሐዋሪያቶች የተገለጠበትን የጴጥሮስ ቤተክርስቲያን ይጎበኛሉ፡፡
 • ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ሁለት ዓሣና አምስት እንጀራ አበርክቶ ያበላበት ታብጋ(Tbgaha) ይጎበኛሉ፡፡ የቅፍርናሆም የመጨረሻ ጉብኝት ሆኖ ምሳ ገበሬዎች መንደር ይሆናል ፡፡ ከምሳ በኋላ ትምምህርተ ወንጌል ና በመዝሙር የታጀበ ጌታ በተመላለሰበት የገሊላ ባህር የጀልባ ላይ ጉዞ በማድረግ መልስ ወደ ሆቴል ይሆናል፡፡

11. ሚያዚያ 24/2014 ዓ.ም ቅዳሜ (April 29 2022)

 • ጎብኚዎች ጥብርያዶስን ለቀው ጉዞ ወደ ሔፋ በቀርሜሎስ ተራራ በማድረግ የነብዩ ኤልያስን ገዳምና ዋሻ ይጎበኛሉ
 • ጉዞ ወደ ቴል አቪቭ ሆን በናታኒያ የገጠር መንደሮች ምሣ ከበሉ በኋላ ጉዞ ወደ ሎድ በማድረግ በሰማዕቱ ቅዱስ ጊዮርጊስ ስም የታነፀውን የግሪክ ኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን ይጎበኛሉ እግረ መንገዳቸውንም አማሁስን ጎብኝተው ጉዞ ወደ ቴል አቪቭ ይሆናል፡፡
 • በቴል አቪቭ የቅዱስ ጱጥሮስ ቤተክርስቲያን የሚገኝበት በኢዮጴ ሐዋርያው ቅዱስ ጴጥሮስ ጣቢታን ከሞት ያስነሳበትን ቅዱስ ስፍራና ፣ የስምዖን ቆዳ ፋቂውን ቤትና ነቢዩ ዮናስ ወደተረሴስ ሲሸሽ በጀልባ የተሳፈረበትን አሮጌውን የጃፋ ደብ ከጎበኙ በኋላ በቴል አቪቭ በተያዘላቸው ሆቴል ክፍላቸውን ተረክበው እረፍት ያደርጋሉ፡፡

12. ሚያዚያ 25/2014 ዓ.ም ዕሁድ  (April 30 2022)

ጎብኚዎች ጧት በ12፡30 ተነስተው በሆቴሉ አዳራሽ በክቡራን አባቶች በሚመራው የፀሎት ፕሮግራም ይሳተፋሉ፡፡ ከቁርስ በኋላ ሙሉ ቀን የእረፍት ቀን ይሆናል ጎብኚዎች የሜድትራሊያን ባህር ዳርቻ በመሄድ ወይም እደፍላጎታቸው በሆቴሉ አቅራቢያ በሚገኘው የገበያ ቦታ በመሄድ ዕለቱን ያሳልፋሉ፡፡ ምሳ እና ዕራት በሆቴሉ ውስጥ

13. ሚያዚያ 26/2014 ዓ.ም ሰኞ  (May 01 2022)

ጧት ወደ እስራኤል ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ጣቢያ ቤን ጎሪዮን አየር ማረፊያ ጉዞ በማድረግ ጎብኚዎች የእስራኤል ቆይታቸውን አጠናቀው ወደ አገራቸው ይመለሳሉ፡፡

ማሳሰቢያ፡– ይህ ፕሮግራም እደሚኖረን ግዜና እንደ እስራኤል ተጨባጭ ሁኔታ ሊቀያየር ይችላል፡፡

የጉዞ ዋጋ ፡- ሁለት መቶ አስር ሺ ብር (210,000)

ክፍያው የሚያካትታቸው

 • 11 ቀን የሆቴል ክፍያ
 • የደርሶ መልስ የአውሮፕላን ትኬት
 • ቁርስ,ምሳ,እራት
 • ሙሉ በእስራኤል ሀገር የሚያስፈልጉትን የትራንስፖረት ወጪዎች
 • የአስጎብኚ
 • የእስራኤል ግሩፕ ቪዛ
 • የጀልባ ክፍያ
 • የቤተክርስቲያን መግቢያ ክፍያዎች
 • ልዩ የሆነ የኮቪድ ኢንሹራንስ

ለጉዞ የሚስፍጉ ነገሮች

 • የኮቪድ 19 ክትባት የወሰዱ መሆን እናም ማረጋገጫ ሰርተፍኬት ማቅረብ የሚችሉ
 • ለመመዝገብ ሲወስኑ የመመዝገቢያ 2000 ብር ክፍያ ይከፍላሉ

ለአአስፈላጊው መረጃ፡- በስልክ ቁጥር 0912805634,0911943133, 0118 359242 እዲሁም ቢሮዓችን ድረስ በአካል መምጣት ለምትፈልጉ ካሳንቺስ ነጋ ሲቲ ሞል 1ኛ ፎቅ